ባህር ዳር ከተማ ከ ሰበታ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የ21ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እነሆ!

ከሁለት ጨዋታ በኋላ ዋና አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝን ያገኘው ባህር ዳር ከተማ በሀዋሳ ከተማ ከተሸነፈው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጓል። በዚህም በግርማ ዲሳሳ እና በረከት ጥጋቡ ምትክ አፈወርቅ ኃይሉ እና ሳለአምላክ ተገኘ በአሰላለፉ ተካተዋል።

በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በኩል ባለፈው ሳምንት ያላገኟቸውን ተጫዋቾች ማግኘት የቻሉ ሲሆን ስድስት ለውጦችም አድርገዋል። ፋሲል ገብረሚካኤል በጎሉ መካከል የምንተስኖት አሎን ቦታ ሲረከብ አዲስ ተስፋዬ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ክሪዚስቶም ንታምቢ፣ መስዑድ መሐመድ እና ፍፁም ገብረማርያም ለዚህ ጨዋታ የመጀመርያ ተሰላፊ የሚሆኑ ተጫዋቾች ናቸው። አንተነህ ተስፋዬ፣ መሳይ ጳውሎስ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ (ቅጣት)፣ ፉአድ ፈረጃ እና አብዱልባሲጥ ከማል ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት የተተኩ ናቸው።

ጨዋታውን ተፈሪ አለባቸው በዋና ዳኝነት ይመራዋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ባህር ዳር ከተማ

1 ፅዮን መርዕድ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
8 ሳምሶን ጥላሁን
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
25 ምንይሉ ወንድሙ

ሰበታ ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
14 ዓለማየሁ ሙለታ
12 ቢያድግልኝ ኤልያስ
21 አዲስ ተስፋዬ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሐመድ
28 ክሪዚስቶም ንታምቢ
7 ቡልቻ ሹራ
11 ናትናኤል ጋንቹላ
77 ኦሰይ ማውሊ
16 ፍፁም ገብረማርያም


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ