ፌዴሬሽኑ ዋልያዎቹን ሊሸልም ነው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለተመለሰው ብሔራዊ ቡድን ሽልማት ሊያበረክት ነው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ በተደረገው ስብሰባ ቀጣዮቹን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1. ከ8 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመለሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የ6 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንዲሰጣቸው እና ሽልማቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማጠቃለያዉን በሚያደርግበት ሐዋሳ ከተማ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።

2. ለክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከ17ዓመት በታች ውድድር ላይ ለሚሰሩት ስራ ድጋፍ የሚሆን የ300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር ) ድጋፍ ለእያንዳንዱ የክልል እና የከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች እንዲሰጥ እና ስራው በአግባቡ ስለመሰራቱ እያንዳንዱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክትትል እንዲያደርግ ተወስኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ