ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኃላ የሚጀምረው የድቻ እና የጊዮርጊስ ጨዋታ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ወላይታ ድቻ ከሰበታ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርጓል። በዚህም ዳንኤል አጄዬ በመክብብ ደገፉ ፣ አበባየሁ አጅሶ በነፃነት ገብረመድህን እንዲሁም ዲዲዬ ለብሪ ደግሞ በኢዙ አዙካ ቦታ ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። ከተጫዋቼች ውጪም አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እንደ ሃያኛው ሳምንት ሁሉ ቡድናቸውን ሜዳ ላይ ተገኝተው እንደማይመሩ ታውቋል።

በርካታ ለውጦች እንደሚኖሩት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ጊዮርግሲ አሰላለፍ ውስጥም አምስት ቅያሪዎች ኖረዋል። የዲስፕሊን ቅጣት የተጣለባቸው አስቻለው ታመነ ፣ ሙሉዓለም መስፍን ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ጌታነህ ከበደ በምንተስኖት አዳነ ፣ የአብስራ ተስፋዬ ፣ አቤል ከበደ እና ሳላዲን ሰዒድ ተተክተዋል። ቡድኑ ባደረገው ሌላው ለውጥ ደግሞ ደስታ ደሙ አብዱልከሪም መሀመድን ተክቶ ጨዋታውን ይጀምራል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ወላይታ ድቻ

30 ዳንኤል አጃዬ
16 አናጋው ባደግ
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
9 ያሬድ ዳዊት
19 አበባየሁ አጅሶ
20 በረከት ወልዴ
6 ጋቶች ፓኖም
11 ዲዲዬ ለብሪ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ
21 ቸርነት ጉግሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
14 ሄኖክ አዱኛ
23 ምንተስኖት አዳነ
6 ደስታ ደሙ
24 ፍሪምፖንግ ሜንሱ
5 ሐይደር ሸረፋ
16 የአብስራ ተስፋዬ
10 አቤል ያለው
21 ከነአን ማርክነህ
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
7 ሳላዲን ሰዒድ


© ሶከር ኢትዮጵያ