አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ድሬዳዋ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል፡፡ ተያያዥ መረጃዎች እና የቡድኖቹን አሰላለፍም እንዲህ አቅርበናል፡፡

የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቡድን ከሀድያ ሆሳዕና አቻ ከተለያዩበት ጨዋታ በሦስት ተጫዋቾች ላይ ለውጥን በማድረግ ኢታሙና ኬሙይኔ፣ ሪችሞንድ አዶንጎ እና ዳንኤል ኃይሉን አሳርፈው እንዳለ ከበደ፣ አስቻለው ግርማ እና ሙኽዲን ሙሳን ወደ አሰላለፉ አካተዋል። አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስም የሀዋሳ ጨዋታቸው የሞት ሽረት እንዲሁም በሊጉ ለመቆየት ወሳኝ ምዕራፎችን የምንጀምርበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ አዳማ ከተማ በድሬዳዋ የመጨረሻ ጨዋታ በፋሲል ከነማ ከተረታበት የመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ ሦስት ለውጦችን በማድረግ ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡ ሲሆን በማማዱ ኩሊባሊ፣ ደሳለኝ ደባሽ እና ሀብታሙ ወልዴ ምትክ ሰይፈ ዛኪር፣ በቃሉ ገነነ እና በላይ ዓባይነህን ተጠቅመዋል። ቡድናቸው መሻሻል ቢኖረውም ውጤት ላይ ግን ደካማ ስለመሆናቸው አሰልጣኝ ዘርዓይ ጠቅሰው በሀዋሳ ቆይታቸው ውጤት ለማምጣት መዘጋጀታቸውንም ከጨዋታው አስቀድሞ በነበራቸው ንግግር ጠቁመዋል፡፡
ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደወ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ይመራል።

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
6 ዐወት ገብረሚካኤል
15 በረከት ሳሙኤል
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
11 እንዳለ ከበደ
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኸዲን ሙሳ
20 ጂኒያስ ናንጂቡ

አዳማ ከተማ

1 ሴኩምባ ካማራ
13 ታፈሰ ሰርካ
44 ትዕግስቱ አበራ
88 አሊሲ ጆናታን
80 ሚሊዮን ሰለሞን
34 ላሚን ኩማራ
25 ኤልያስ ማሞ
8 በቃሉ ገነነ
27 ሰይፈ ዛኪር
10 አብዲሳ ጀማል
9 በላይ ዓባይነህ


© ሶከር ኢትዮጵያ