የሀዲያ ሆሳዕና ክለብ እና ተጫዋቾቹ ጉዳይ ወደ ሽምግልና አምርቷል

በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመዳኘት እየመረመረ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን በሽምግልና መያዙ ታውቋል።

በሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ እና በአስራ አምስቱ ተጫዋቾች መካከል ለወራት የከረመ አለመግባባት ኋኃላ ላይ ከሁለቱም ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ ውሳኔዎች ምክንያት እየተካረረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ ወደ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳመራ ይታወቃል።

አሁን ደግሞ ባሳለፍነው ረቡዕ የፌዴሬሽኑ የህግ ባለሙያ ክፍል ሁለቱንም አካላት በመጥራት ስለጉዳዩ ዝርዝር ነገሮችን በተናጥል እንዲያስረዱ ካደረገ በኋላ ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት ለፊታችን ረቡዕ የመጨረሻ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ረቡዕ በሚኖረው የሁለቱ አካላት ውይይት ከስምምነት በመድረስ በመሀከላቸው ተፈጥሮ የነበረው ችግር ለመጨረሻ ጊዜ ይቀረፉ ይሆን የሚለው ተጠባቂ ሆኗል።

ያጋሩ