​ወልቂጤ አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በህመም ምክንያት ከቡድኑ መራቃቸውን ተከትሎ ወልቂጤዎች አዲስ አሰልጣኝ ማግኘታቸው ታውቋል።

አስቀድመው በሰበሰበሰቡት ነጥብ ካልሆነ በቀር ከሁለተኛው ዙር ከጅማሮ አንስቶ የውጤት መሸራተት ላይ የሚገኙት ወልቂጤዎች በድሬዳዋው ቆይታቸው አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በጤና እክል ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙ በኋላ እስካሁን ቡድኑን እየመሩ እንደማይገኝ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የቡድን አባላት በልምምድ ሜዳ ተገኝተው አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ ልምምድ ሲያሰሩ መቆየታቸውን አረጋግጠናል። የአሰልጣኝ ሲሳይ ቅጥር በቋሚነት አልያም በጊዛዊነት ይሁን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜ አልተሳካ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ