ወልቂጤ ከተማ ሦስት ተጫዋቾቹን ከቡድኑ ገለል አድርጓል

ላለመውረድ እየታገሉ የሚገኙት ሠራተኞቹ “አላስፈላጊ ቦታ ተገኝተዋል” ያሏቸው ሦስት ተጫዋቾችን ከቡድኑ ካምፕ አስወጥተዋል።

ከሰዓታት በፊት አሠልጣኝ ሲሳይ አብርሃን በአሠልጣኝነት የሾሙት ወልቂጤ ከተማዎች “የዲሲፕሊን ጥሰት ፈፅመው ተገኝተዋል” ያሏቸው ሦስት ተጫዋቾቻቸውን ከቡድኑ ካምፕ ማስወጣታቸው ተረጋግጧል። ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ መሠረትም ተጫዋቾቹ ፍሬው ሰለሞን፣ ይበልጣል ሽባባው እና አዳነ በላይነህ ናቸው። ስማቸው የተጠቀሰው እነኚህ ሦስት ተጫዋቾችም ለጊዜው ከልዑኩ እንዲወጡ ቢደረግም በቀጣይ የክለቡ የሥራ አመራር ቦርድ ከተጫዋቾቹ ጋር የሚያደርገው ንግግር እና የሚወስነው ውሳኔ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ