የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተራዝመዋል

ከግንቦት ወር መጀመሪያ አንስቶ ሊደረጉ የነበሩት የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች መራዘማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ እንዳረጋገጠ አስታውቋል።

“በሞሮኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች መራዘማቸውን ካፍ አስታወቀ። ግንቦት 30/2013 የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዩጋንዳ አቻው ለመጫወት በካፍ አካዳሚ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የሉሲዎቹ ስብስብ በቀጣይ ዓመት በጥቅምት ወር ጨዋታውን እንደሚያደርግ ታውቋል። ካፍ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማራዘሙ ምክንያት ያደረጋቸው ነጥቦች የስታዲየሞች በካፍ ክለብ ላይሰንሲግ መስፈርት በአግባቡ አለመዘጋጀት እና የኮቪድ ጉዳይ መሆናቸው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በካፍ እካዳሚ ያለውን ዝግጅት በነገው ዕለት እንደሚያቆም ታውቋል።”