የረፋዱ ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላሉ።
ባሳለፍነው ሳምንት ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ካጠናቀቁት ሁለቱ ቡድኖች ውስጥ ጅማ አባ ጅፋር በስብስቡ ላይ ለውጥ ላለማደርግ ሲወስን ባህር ዳር ከተማ ሁለት ቅያሪዎችን አድርጓል።
በለውጦቹ ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ በሀሪሰን ሄሱ ቦታ ጨዋታውን ሲጀምር ባዬ ገዛኸኝም ወሰኑ ዓሊን ተክቶ ወደ ቀዳሚው አሰላለፍ መጥቷል።
ጨዋታውን አስመልክቶ በተሰጡ አስተያየቶች አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ቡድናቸው የተሻሻሉ ነገሮች እንዳሉት እና በአሰላለፍ ላይ ብዙ ለውጥ አለማድረጋቸውን ጠቅሰው በሒሳባዊ ስሌት ወደ 11ኛ ደረጃ ለመምጣት እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። የባህር ዳሩ አቻቸው አሰልጣኝ ፋሲል ተካል በበኩላቸው በነፃነት ከሚጫወት ቡድን ጋር መጫወት አስቸጋሪ መሆኑን ሳይሸሸጉ ጨዋታውን ማሸነፍ ለቡድናቸው ያለውን አስፈላጊነት ጠቁመዋል።
ፌደራል ዳኛ ባህሩ ተካ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-
ጅማ አባ ጅፋር
91 አቡበከር ኑሪ
28 ሥዩም ተስፋዬ
4 ከድር ኸይረዲን
16 መላኩ ወልዴ
8 ሱራፌል ዐወል
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
24 ዋለልኝ ገብሬ
20 ሀብታሙ ንጉሤ
15 ዋውንጎ ፕሪንስ
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ
ባህር ዳር ከተማ
1 ፅዮን መርዕድ
13 አህመድ ረሺድ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
18 ሣለአምላክ ተገኘ
12 በረከት ጥጋቡ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
14 ፍፁም ዓለሙ
7 ግርማ ዲሳሳ
25 ምንይሉ ወንድሙ
9 ባዬ ገዛኸኝ