​ለሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት 30 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዩጋንዳን ግንቦት መጨረሻ ላይ የሚገጥሙት ሉሲዎቹ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

አመዛኞቹ ተጫዋቾች ባለፈው ወር ደቡብ ሱዳንን የገጠመው ስብስብ አካል የነበሩ ሲሆን አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ካለፈው ምርጫ ለውጥ የተደረገባቸው ናቸው።

ቡድኑ ከእሁድ ጀምሮ በካፍ አካዳሚ ዝግጅት እንደሚጀምር ይጠበቃል። 

ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (መከላከያ)፣ ንግስት መዓዛ (ንግድ ባንክ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)፣ ቤተልሔም ዮሐንስ (አዲስ አበባ ከተማ) 

ተከላካዮች

ታሪኳ ዴቢሶ (ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ንግድ ባንክ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ንግድ ባንክ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ሳራ ኪዶ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ትዝታ ኃ/ሚካኤል (ሀዋሳ ከተማ)፣ መስከረም ካንኮ (መከላከያ)፣ አሰቤ ሙሶ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፀሀይነሽ በቀለ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ እፀገነት ብዙነህ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (ንግድ ባንክ)፣ ሰናይት ቦጋለ (ንግድ ባንክ)፣ ህይወት ደንጊሶ (ንግድ ባንክ)፣ አረጋሽ ካልሳ (ንግድ ባንክ)፣ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ (ንግድ ባንክ)፣ ትግስት ያደታ (ንግድ ባንክ)፣ ኤደን ሽፈራው (መከላከያ)፣ መሳይ ተመስገን (መከላከያ)፣ ማዕድን ሳህሉ (ድሬዳዋ ከተማ)

አጥቂዎች 

ሎዛ አበራ (ንግድ ባንክ)፣ ሴናፍ ዋቁማ (መከላከያ)፣ መሳይ ተመስገን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ንግስት በቀለ (ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ)፣ ፀጋነሽ ወራና (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

ያጋሩ