አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ

ከ23ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እነሆ!

ከ2013 ፕሪምየር ሊግ መውረዱን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ጀሚል ያዕቆብ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ አሚን ነስሩ፣ ደሳለኝ ደባሽ፣ ሀብታሙ ወልዴ እና ኤልያስ አህም ወደ አሰላለፉ መጥተዋል። ላሚን ኩማራ (ቅጣት)፣ ትዕግስቱ አበራ፣ አሊሲ ጆናታን፣ ኤልያስ ማሞ፣ ሰይፈ ዛኪር እና በላይ ዓባይነህ ከላይ በተጠቀሱት የተተተኩ ተጫዋቾች ሆነዋል። ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እንደሚጫወቱ የገለፁት አሰልጣኝ ዘርዓይ ከወረዱበት ለመመለስ ቀጣዩ ዕድል ስላለ እሱን አስበው እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሌሎች ተፎካካሪዎች ነጥብ በመጣላቸው ወደ ሁለተኛ ደረጃ የመጠጋት አጋጣሚ የተፈጠረለት ሀዋሳ ከተማ ሆሳዕናን ከረታው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ቸርነት በአወሽ፣ ዳዊት ታደሰ እና ኤፍሬም ዘካርያስ ምትክ ተባረክ ሄፋሞ፣ ሄኖክ ድልቢ እና አለልኝ አዘነን ወደ አሰላለፍ አምጥቷል። በተሻለ ደረጃ ለመጨረስ የቀሩትን ጨዋታ በማሸነፍ ላይ ተመስርተው እንደሚጫወቱ የተናገሩት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረት መውረዱን ያረጋገጠ ቡድን በነፃነት ስለሚጫወት ለዛ ዝግጅት እንዳደረጉ ገልፀዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ተካልኝ ለማ ይመራዋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-

አዳማ ከተማ

1 ሴኩምባ ካማራ
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጊቻሞ
28 አሚን ነስሩ
80 ሚሊዮን ሰለሞን
22 ደሳለኝ ደባሽ
26 ኤልያስ አህመድ
8 በቃሉ ገነነ
5 ጀሚል ያዕቆብ
29 ሀብታሙ ወልዴ
10 አብዲሳ ጀማል

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
14 ብርሀኑ በቀለ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
23 አለልኝ አዘነ
25 ሄኖክ ድልቢ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
10 መስፍን ታፈሰ
20 ተባረክ ሄፋሞ

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ