አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሀዋሳ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

የመጨረሻው ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል።

በሀዋሳ ከተማ በኩል ከፋሲል ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ እና ተባረክ ሔፋሞ ምትክ ምንተስኖት ጊምቦ፣ ብሩክ በየነ እና አዲስዓለም ተስፋዬ የሚጫወቱ ይሆናል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትም የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ደረጃቸው እንደሚሻሻል በመግለፅ አሽንፈው እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት አራፊ በነበረው ድሬዳዋ በኩል የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ ተደርጓል። ፍሬው ጌታሁን፣ በረከት ሳሙኤል፣ ሱራፌል ጌታቸው፣ አስቻለው ግርማ፣ ሙኸዲን ሙሳ እና ኢታሙና ኬሙይኔ አርፈው ወንድወሰን አሸናፊ፣ ሚኪያስ ካሣሁን፣ ሄኖክ ገምቴሳ፣ ረመዳን ናስር፣ ሳሙኤል ዘሪሁን እና ቢንያም ጥዑመልሳን በአሰላለፉ ተካተዋል። ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ዋነኛ ዕቅዳቸው በመሳካቱ የዛሬውን ጨዋታ እንደወዳጅነት ጨዋታ እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።

ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ለመምራት ፌዴራል ዳኛ ተፈሪ አለባቸው ተመድበዋል።

ቡድኖቹ ለዛሬ የመረጡት የመጀመሪያ አሰላለፍ :-

ሀዋሳ ከተማ

99 ምንተስኖት ጊምቦ
14 ብርሀኑ በቀለ
6 አዲስዓለም ተስፋዬ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
23 አለልኝ አዘነ
18 ዳዊት ታደሰ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
17 ብሩክ በየነ
21 ኤፍሬም አሻሞ
10 መስፍን ታፈሰ

ድሬዳዋ ከተማ

90 ወንድወሰን አሸናፊ
6 ዐወት ገብረሚካኤል
44 ሚኪያስ ካሣሁን
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
9 ሄኖክ ገምቴሳ
10 ረመዳን ናስር
77 ሳሙኤል ዘሪሁን
7 ቢንያም ጥዑመልሳን
22 ሪችሞንድ አዶንጎ

ያጋሩ