የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ አሰናድተናል።
በአዳማ ከተማ በኩል በሰበታ ከተማ ከተሸነፈው ስብስብ የአምስት ተጫዋች ለውጥ በማድረግ ታፈሰ ሰርካ፣ አሚን ነስሩ፣ ኤልያስ ማሞ፣ ማማዱ ኩሊባሊ እና ሀብታሙ ወልዴ አርፈው ጀሚል ያዕቆብ፣ ላሚን ኩማሬ፣ በላይ ዓባይነህ፣ ብሩክ መንገሻ እና ሰይፈ ዛኪር ወደ አሰላለፉ መጥተዋል። አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በነፃነት እንደሚጫወቱ ተናግረው ፋሲልን እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በሀዲያ ሆሳዕና ሽንፈት ካስተናገደው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ደስታ ደሙ እና አቤል እንዳለ አርፈው አማኑኤል ተርፉ እና ሳላዲን በርጊቾ (ለመጀመርያ ጊዜ) ተተክተዋል። ፋሲልን እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት ያስተላለፉት አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደተዘጋጁ ገልፀዋል።
ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ተካልኝ ለማ ይመራዋል።
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-
አዳማ ከተማ
1 ሴኩምባ ካማራ
5 ጀሚል ያዕቆብ
34 ላሚን ኩማሬ
20 ደስታ ጊቻሞ
80 ሚሊዮን ሰለሞን
88 ኢሊሴ ጆናታን
8 በቃሉ ገነነ
9 በላይ ዓባይነህ
18 ብሩክ መንገሻ
27 ሰይፈ ዛኪር
10 አብዲሳ ጀማል
ቅዱስ ጊዮርጊስ
22 ባህሩ ነጋሽ
3 አማኑኤል ተርፉ
13 ሳላዲን በርጊቾ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
14 ሄኖክ አዱኛ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሐይደር ሸረፋ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
7 ሳላዲን ሰዒድ