አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ባህር ዳር ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

የረፋዱ ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላሉ።
የውድድር ዓመቱን የመጨረሻ ጨዋታ የሚያደርጉት ባህር ዳር ከተማዎች በአራት ተጫዋቾች ላይ ለውጥ በማድረግ በረከት ጥጋቡ፣ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ ፍፁም ዓለሙ እና ምንይሉ ወንድሙ አርፈው ይበልጣል አየለ፣ ደረጄ መንግሥቱ፣ ሳምሶን ጥላሁን እና አፈወርቅ ኃይሉ በአሰላለፉ ተካተዋል። አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝም በጥሩ ውጤት ዓመቱን ለማገባደድ አልመው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልፀዋል።

የቀሩትን ሁለት ጨዋታዎች ለማሸነፍ እንደተዘጋጁ የገለፁት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከጅማው ጨዋታ የሦስት ተጫዋችች ለውጥ አድርገው ፀጋዬ ብርሀኑ፣ አንተነህ ጉግሳ እና ነፃነት ገብረመድህንን በማሳረፍ በረከት ወልዴ፣ ኢዙ አዙካ እና ዮናስ ግርማይን አካተዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሤ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ባህር ዳር ከተማ

22 ፅዮን መርዕድ
13 አህመድ ረሺድ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
7 ግርማ ዲሳሳ
4 ደረጄ መንግሥቱ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
8 ሳምሶን ጥላሁን
20 ይበልጣል አየለ
18 ሣለአምላክ ተገኘ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ወላይታ ድቻ

30 ዳንኤል አጃዬ
16 አናጋው ባደግ
2 ደጉ ደበበ
7 ዮናስ ግርማይ
9 ያሬድ ዳዊት
20 በረከት ወልዴ
8 እንድሪስ ሰዒድ
6 ጋቶች ፓኖም
23 ኡዙ አዙካ
21 ቸርነት ጉግሳ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ

ያጋሩ