አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ፋሲል ከነማ ከ ሀዋሳ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናቸዋል።

የግላቸው ያደረጉትን ዋንጫ በዛሬው ዕለት የሚረከቡት ፋሲል ከነማ ከ19 ጨዋታዎች በኋላ ከተሸነፉበት የድሬዳዋው ፍልሚያ ስምንት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሰዒድ ሀሰን፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ሽመክት ጉግሳ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ፍቃዱ ዓለሙን በማሳረፍ ሳማኬ ሚኬል፣ ሄኖክ ይትባረክ፣ ይሁን እንዳሻው፣ አቤል እያዩ፣ ዓለምብርሀን ይግዛው፣ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ፣ በዛብህ መለዮ እና ዳንኤል ዘመዴ ወደ ቋሚ አሰላለፍ አምጥተዋል። ከወልቂጤ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋሩ በኋላ ዛሬ ወደ ሜዳ የሚገቡት ሀዋሳዎች ደግሞ ዳግም ተፈራን በሜንሳህ ሶሆሆ እንዲሁም ተባረክ ሔፉሞን በዳንኤል ደርቤ ብቻ ለውጠው ለጨዋታው ቀርበዋል።

አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ከጨዋታው መጀመር በፊትም ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ በርከት ያሉ ደጋፊዎቻቸውን በሜዳ በማየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትም የሀዋሳም ሆነ የፋሲል ደጋፊዎች በሜዳው መገኘታቸው ጥሩ እንደሆነ አንስተዋል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በላይ ታደሰ ተመድበዋል።

ቡድኖቹ ለዛሬ የመረጡት የመጀመሪያ አሰላለፍ :-

ፋሲል ከነማ

1 ሳማኬ ሚኬል
2 እንየው ካሣሁን
25 ዳንኤል ዘመዴ
16 ያሬድ ባየህ
3 ሄኖክ ይትባረክ
8 ይሁን እንዳሻው
24 አቤል እያዩ
17 በዛብህ መለዮ
27 ዓለምብርሀን ይግዛው
18 ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ
26 ሙጂብ ቃሲም

ሀዋሳ ከተማ

22 ዳግም ተፈራ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
20 ተባረክ ሔፉሞ
23 አለልኝ አዘነ
18 ዳዊት ታደሰ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
10 መስፍን ታፈሰ
14 ብርሀኑ በቀለ