የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ አሰናድተናል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፈው ሳምንት አዳማ ከተማን ከረታው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በሳላዲን ሰዒድ እና አቤል ያለው ምትክ ዳግማዊ አርዓያ እና ከነዓን ማርክነህን የሚያሰልፍ ይሆናል። በሀዋሳ ቆይታቸው ደስተኛ እንደሆኑ የገለፁት አሰልጣኝ ፍራንክ ናታልም ለጨዋታው ትኩረት ሰጥተው እንደሚገቡ ተናግረዋል።
በወልቂጤ በኩል በሰበታ ከተሸነፉበት ያለፈው ሳምንት ስብስብ በያሬድ ታደሰ፣ ሄኖክ አየለ፣ ዮናታን ፍስሐ እና ሀብታሙ ሸዋለም ምትክ አህመድ ሁሴን፣ አሜ መሐመድ፣ በኃይሉ ተሻገር እና ዮናስ በርታን ተክተዋል። አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም ለማሸነፍ ወደሜዳ እንደሚገቡ ገልፀዋል።
ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ይመራዋል።
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-
ቅዱስ ጊዮርጊስ
22 ባህሩ ነጋሽ
3 አማኑኤል ተርፉ
13 ሳላዲን በርጊቾ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
14 ሄኖክ አዱኛ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሐይደር ሸረፋ
21 ከነዓን ማርክነህ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
19 ዳግማዊ አርዓያ
ወልቂጤ ከተማ
1 ጀማል ጣሰው
30 ቶማስ ስምረቱ
4 መሐመድ ሻፊ
3 ረመዳን የሱፍ
15 ዮናስ በርታ
25 ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
18 በኃይሉ ተሻገር
10 አህመድ ሁሴን
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሐመድ