“ዝቅ ባለ ሀሳብ ላይ አስተያየት አልሰጥም …” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ሰሞኑን መነጋገርያ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ የሊግ ካምፓኒው ፕሬዝደንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል።

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ከበርካታ ስኬቶቹ እና መሻሻል ከሚገባቸው ድክመቶቹ ጋር በዛሬው ዕለት መጠናቀቁ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም የሊግ ካምፓኒው ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት የኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ 60% በSMS እንደሚሰጥ እና የቀረው 40% በራሱ አወዳዳሪው አካል ምርጫው እንደሚካሄድ ቢገለፅም ይህ ተግባራዊ ሳይደረግ የፊታችን ሰኞ ምርጫው ተጠናቆ ይፋ እንዲደረግ መታሰቡን ሰምተናል። እንዲሁም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው ለሚያጠናቅቁ ቡድኖች ምንም ዓይነት የሜዳልያ ሽልማት እንደማይሰጥ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ለደረጃ ፈፃሚ ክለቦች የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቷል። የትግራይ ክለቦች ክለቦች ካልተሳፉ ቀጣዩ የውድድር ዘመን እንዴት ይሆናል በሚለው ዙርያም ካምፓኒው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሒደሁን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያወጣው መግለጫ ደግመሞ ከዛ በተቃራኒ ሆኗል።

በነዚህ ከጋዜጣዊ መግለጫው ጋር ልዩነት በታየባቸው ጉዳዮች እና የፌዴሬሽኑ መግለጫ ዙርያ የሊግ ካምፓኒው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞን ጠይቀን ተከዩን ምላሽ ሠጥተዋል።

ስለ ኮኮቦች ምርጫ…

60% በስፖርት ቤተሰቡ ድምፅ ይካሄዳል ስለማለቴ አላስታውስም። ሆኖም የሊግ ካምፓኒው የውድድር ሥነ ስርዓት ኮሚቴ የተሻለ ነው በሚለው መንገድ የኮከብ ምርጫውን ለማካሄድ አስቧል። በዚህም መሰረት ምርጫው አጠናቆ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የሜዳልያ ሽልማት…

በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይህ ሽልማት እንደማይኖር መናገሬን አውቃለሁ። ይህ የእኔ ስህተት ተደርጎ ይወሰድ። ሁኔታዎችን በድጋሚ በማጤን ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው ለጨረሱ ሜዳሊያ ለመሸለም ችለናል።

የፌዴሬሽኑ አቋም…

እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ማባከን አልፈልግም። አስቀድሞ ለአቋም መግለጫ ፌስቡክ ላይ ከመሮጥ መነጋገር አስፈላጊ ነው። ሲሆን ሲሆን ሳትጫጯህ መነጋገር ነው። ሊግ ካምፓኒው ከፌዴሬሽኑ በታች መሆኑ ይታወቃል። የሊግ ካምፓኒው የሥራ ድርሻ ምን እንደሆነ ግልፅ ነው። ያም ቢሆን በጣም ዝቅ ባለ ሀሳብ ላይ አስተያየት አልሰጥም፤ ጊዜዬንም ማጥፋት አልፈልግም። ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የሊግ ውድድሮች የሚመሩት በምን እንደሆነ ይታወቃል። እኛም እዛ እስክንደርስ ድረስ ጫጫታዎች ይኖራሉ። በጠቅላላ ጉባኤያችን ይህን ጉዳይ አንስተንም የምናወራ አይሆንም። እኛ አስተያየታችንን ሰጥተናል። ከዚህ ውጭ የሚፈፀሙ ነገሮች ካሉ ደግሞ የምናየው ይሆናል።

ስለ አዲሱ ዋንጫ…

ዋንጫው ከሀገር ውስጥም ይምጣ ከውጪ ሲመጣ የምታዩት ይሆናል።

የፌዴሬሽኑ መግለጫ ይህ ነበር :-