የረፋዱ ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላሉ።
በወላይታ ድቻ በኩል ከባህር ዳሩ ድል የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በደጉ ደበበ እና ዮናስ ግርማይ ምትክ ነፃነት ገብረመድኅን እና አንተነህ ጉግሳ ተካተዋል። የተሻለ ደረጃ ይዞ ለመጨረስ አልመው እንደሚገቡ የተናገሩት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ነፃ ጨዋታ እንደሚሆን ተንብየዋል።
በሲዳማ ቡና በኩል ጅማን ካሸነፈው ስብስብ የአምስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በአማኑኤል እንዳለ፣ ሰንደይ ሙቱኩ፣ ያሳር ሙገርዋ፣ ብርሀኑ አሻሞ እና ቢንያም በላይ ምትክ ዮሴፍ ዮሐንስ፣ ጊት ጋትኩት፣ ግሩም አሰፋ፣ ይገዙ ቦጋለ እና አበባየሁ ዮሐንስ የሚሰለፉ ይሆናል። አሁል በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የተገለፁት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ጨዋታው ግን ጠንካራ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-
ወላይታ ድቻ
30 ዳንኤል አጃዬ
16 አናጋው ባደግ
26 አንተነህ ጉግሳ
20 በረከት ወልዴ
9 ያሬድ ዳዊት
32 ነፃነት ገብረመድኅን
8 እንድሪስ ሰዒድ
6 ጋቶች ፓኖም
23 ኡዙ አዙካ
21 ቸርነት ጉግሳ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ
ሲዳማ ቡና
1 ፍቅሩ ወዴሳ
12 ግሩም አሰፋ
24 ጊት ጋትኩት
19 ግርማ በቀለ
5 መሐሪ መና
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
10 ዳዊት ተፈራ
21 አበባየሁ ዮሐንስ
26 ይገዙ ቦጋለ
8 ኢኪኪ አፎላቢ
27 ማማዱ ሲዲቤ