የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 1-1 አዳማ ከተማ

ከረፋዱ ጨዋታ በመቀጠል ተጋጣሚ አሰልጣኞች ሀሳባቸውን ለሱፐር ስፖርት አካፍለዋል።

አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለቡድናቸው የጨዋታ ዕድገት

ጥሩ ነገር አለ ፤ የሚታረሙ ብዙ ነገሮችም አሉ። ግን ከነስህተታችን ሆነን ደግሞ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው የሚታዩ ጥሩ ነገሮች አሉ። ስለዚህ አጠቃላይ ሥራችንን ማረሙ እንዳለ ሆኖ ባለው ነገር ደስተኛ ነኝ።

ስለቀጣይ ዓመት

የሚሰሩትን ስህተቶች ብናርም የተሻለ ነገር ማድረግ ስለሚቻል ማረም የግድ ነው የሚሆነው። መቀነስ አለብን ፤ ምንአልባት አንዳንድ ጊዜ በእግር ኳስ ውስጥ መቶ በመቶ ስህተቶችን ማስወገድ ከባድ ሊሆን ይችላል። ግን መቀነስ የምንችላቸው ስህተቶች ስላሉ እነሱን መቀነስ አለብን ብዬ አስባለሁ። ያ ከሆነ የተሻለ ነገር ይኖራል።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – አዳማ ከተማ

ስለጨዋታው

ጨዋታው ዛሬ እጅግ በጣም ጥሩ ነበር። በምፈልገው መንገድ ተንቀሳቅሰናል ታክቲካሊ ጥሩ ነበሩ። ብዙ አጋጣሚዎችን አልተጠቀምንም እንጂ ከዕረፍት በኋላ ሦስት አራት የሚሆኑ ኳሶችን አባክነናል ፤ ያው ኳስ ነው። ግን ዘጠናውንም ደቂቃ ማለት ይቻላል ዛሬ ተጭነን ተጫውተናል። ስንከላከልም ጥሩ ነበርን። ያው አቻው ባይገባንም እንቀበለዋለን። ባለቀ ሰዓት ትኩረት የማጣት ጉዳይ ነው። በተደጋጋሚ ቅጣት ምቶች ሲሰጡ የመውረድ ሁኔታ ይታይብናል። ተጫዋቹም ተጎድቶ ወጥቶ ስለነበር መነፋት ነበረበት ፤ ያው የዳኛ ውሳኔ ነው። በዛ መሀል ነው ኳሱ ቆመ ፤ በአቋቋም ችግር ገብቶብናል። ያው እንቀበላለን። ግን ተጫዋቾቹ ያደረጉት ተጋድሎ በጣም ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል።