አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ

የውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ቀን የረፋድ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ አሰናድነተናል።

የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚጫወተው ኢትዮጵያ ቡና ሀዲያ ሆሳዕናን ካሸነፈው ስብስብ ምንም ለውጥ ሳያደርግ የሚገባ ሲሆን ውጤቱ ስለሚያስፈልጋቸው ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡም አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ገልፀዋል።

በአዳማ ከተማ በኩል በቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሸነፈው ስብስብ የአራት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በሴኮባ ካማራ፣ ላሚን ኩማሬ፣ ብሩክ መንገሻ እና ሰይፈ ዛኪር ምትክ ዳንኤል ተሾመ፣ እዮብ ማቲያስ፣ ላውረንስ ኤድዋርድ እና ደሳለኝ ደባሽ ተተክለዋል። አዳዲስ ነገር በመሞከር ጨዋታውን አሸንፈው ደረጃ ለማሻሻል እንደተዘጋጁ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ተናግረዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ቢንያም ወርቃገኘሁ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-

ኢትዮጵያ ቡና

1 ተክለማርያም ሻንቆ
11 አሥራት ቱንጆ
22 ምንተስኖት ከበደ
2 አበበ ጥላሁን
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
13 ዊልያም ሰለሞን
25 ሀብታሙ ታደሰ
7 ሚኪያስ መኮንን
10 አቡበከር ናስር

አዳማ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
20 ደስታ ጊቻሞ
35 ላውረንስ ኤድዋርድ
80 ሚሊዮን ሰለሞን
6 እዮብ ማቲያስ
5 ጀሚል ያዕቆብ
22 ደሳለኝ ደባሽ
88 ኢሊሴ ጆናታን
8 በቃሉ ገነነ
9 በላይ ዓባይነህ
10 አብዲሳ ጀማል

ያጋሩ