አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ጅማ አባ ጅፋር ከ ሀዲያ ሆሳዕና

የውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላል።

12ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ያረጋገጠው ጅማ አባ ጅፋር ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ቡና ከተረታበት ስብስብ ከአራት ተጫዋቾች በቀር ለውጥ አድርጎ ገብቷል። በዚህም ወንድማገኝ ማርቆስ፣ ዋለልኝ ገብሬ፣ መላኩ ወልዴ እና ተመስገን ደረሰ ብቻ ካለፈው ሳምንት ለውጥ ያልተደረገባቸው ተጫዋቾች ሆነዋል። ውድድሩን በጥሩ ሁኔታ ለመጨረስ ወደ ሜዳ እንደሚገቡም አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ገልፀዋል።

በሀዲያ ሆሳዕና በኩል በቡና ከተሸነፈው ስብስብ የአንድ ተጫዋች ብቻ ለውጥ በማድረግ በፀጋሰው ድማሙ ምትክ እሸቱ ግርማን የሚያሰልፍ ይሆናል። አሰልጣኝ ኢያሱ መርሐፅድቅም ከተጋጣሚያቸው በተሻለ ውጤቱን እንደሚፈልጉት ገልፀዋል።

ፌዴራል ዳኛ ሚካኤል ጠዓመ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ጅማ አባ ጅፋር

99 በረከት አማረ
2 ወንድማገኝ ማርቆስ
25 ኢዳላሚን ናስር
23 ውብሸት ዓለማየሁ
22 ሳምሶን ቆልቻ
6 አማኑኤል ተሾመ
18 አብርሀም ታምራት
24 ዋለልኝ ገብሬ
11 ቤካም አብደላ
19 ተመስገን ደረሰ

ሀዲያ ሆሳዕና

1 ያሬድ በቀለ
74 ቃለአብ ውብሸት
28 እሸቱ ግርማ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
17 ሄኖክ አርፌጮ
48 ክብረዓብ ያሬድ
11 ሚካኤል ጆርጅ
29 እንዳለ ዓባይነህ
7 ዱላ ሙላቱ
12 ዳዋ ሆቴሳ
26 ደስታ ዋሚሾ

ያጋሩ