አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሰበታ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

የከሰዓቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ እነዚህን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።

ምክትል አሰልጣኝ ይታገሱ ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለተሰጣቸው ዕድል አሰልጣኝ አብርሀምን በማመስገን ትምህርት ለማግኘት ሲሉ የእሳቸው ምክትል ለመሆን መምረጣቸውን ተናግረዋል። ቡድኑ ወልቂጤን ከረታበት ጨዋታ በርካታ ለውጦችን ሲያደርግ ሰለሞን ደምሴ ፣ አዲሱ ተስፋዬ ፣ ያሬድ ሀሰን ፣ አብዱልባስጥ ከማል ፣ አብድልሀቪዝ ቶፊቅ ፣ ቃልኪዳን ዘላለም እና ዱሬሳ ሹቢሳ ወደ ቀዳሚው አሰላለፍ ሲመጡ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ኃይለሚካኤል አደፍርስ ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ክሪዚስቶም ንታንቢ ፣ ፍፁም ገብረማርያም እና ቡልቻ ሹራ አርፈዋል።

ቻምፒዮኖቹ አብዛኞቹ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ባልያዙበት የመጨረሻ ጨዋታ ስድስት ለውጦችን በማድረግ ጨዋታውን ይጀምራሉ። በዚህም ይድነቃቸው ኪዳኔ ፣ ሰዒድ ሀሰን ፣ ከድር ኩሊባሊ ፣ መጣባቸው ሙሉ ፣ ኪሩቤል ኃይሉ እና በረከት ደስታ ወደ ሜዳ ይገባሉ። በእነሱ የተተኩት ደግሞ ሚካል ሳማኬ ፣ ያሬድ ባየህ ፣ እንየው ካሳሁን ፣ ይሁን እንዳሻው ፣ አቤል እያዩ እና ሙጂብ ቃሲም ሆነዋል። አሰልጣኝ ስየም ከበደ በአዲስ አበ ባ ቆይታቸው መደሰታቸውን እና ኢትዮጵያዊነት የተንፀባረቀበት እንደነበርም ጠቁመዋል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ፌደራል ዳኛ ባህሩ ተካ ተመድበዋል።

ቡድኖቹ ለዛሬ የመረጡት የመጀመሪያ አሰላለፍ :-

ሰበታ ከተማ

30 ሰለሞን ደምሴ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
13 መሳይ ጳውሎስ
21 አዲሱ ተስፋዬ
24 ያሬድ ሀሰን
29 አብዱልባስጥ ከማል
8 ፉአድ ፈረጃ
15 አብዱልሀዚዝ ቶፊቅ
20 ቃልኪዳን ዘላለም
27 ድሬሳ ሹቢሳ
77 ኦሰይ ማውሊ

ፋሲል ከነማ

30 ይድነቃቸው ኪዳኔ
13 ሰዒድ ሀሰን
25 ዳንኤል ዘመዴ
5 ከድር ኩሊባሊ
3 ሄኖክ ይትባረክ
6 ኪሩቤል ኃይሉ
15 መጣባቸው ሙሉ
17 በዛብህ መለዮ
27 ዓለምብርሀን ይግዛው
7 በረከት ደሰታ
18 ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ