የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ገንዘባቸውን ተቀብለዋል

በአሁኑ ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተከናወነ ባለው ፕሮግራም ላይ ክለቦች በገንዘብ ክፍፍሉ ያገኙትን ድርሻ ተቀብለዋል።

ከአንድ ሰዓት ከሠላሳ ጀምሮ የዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር የመዝጊያ ሥነ-ስርዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል። ፕሮግራሙ ላይም የሊጉ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሠብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ለክለቦች በአጠቃላይ 79 ሚሊየን ብር ማበርከት ጀምረዋል። ክለቦችም በተወካዮቻቸው እንደየ ደረጃቸው ተከታዩን ገንዘብ በቼክ ተቀብለዋል።

– አዳማ ከተማ – 5,067,485.08
– ጅማ አባ ጅፋር – 5,244,938.13
– ወልቂጤ ከተማ- 5,442,391.17
– ድሬዳዋ ከተማ – 5,599,844.21
– ሲዳማ ቡና – 5,777,297.26
– ወላይታ ድቻ – 5,954,750.30
– ባህር ዳር ከተማ- 6,132,203.34
– ሀዋሳ ከተማ – 6,309,656.39
– ሰበታ ከተማ – 6,487,109.43
– ሀዲያ ሆሳዕና – 6,664,562.47
– ቅዱስ ጊዮርጊስ – 7,342,015.52
– ኢትዮጵያ ቡና – 7,719,468.56
– ፋሲል ከነማ – 8,196,920.61

የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በአጠቃላይ ከክፍፍሉ ከደረሳቸው ላይ ቅድሚያ የተከፈላቸው ተቀናሽ መደረጉ ይታወቃል።