ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዝግጅት ኢትዮጵያ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገች።

የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት የእግርኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ እየተመራ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል። ወደ አፍሪካ ዋንጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲያልፍ የቡድኑ አባላት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል እድሜያቸው በብሔራዊ ቡድኑ እንዲካተቱ የሚፈቅድላቸው 5 ተጫዋቾች በዚህ ምርጫ የሚካተቱ ሲሆን ቡድኑ ልምምድ ከጀመረ ሰባት ቀናት በኋላ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ የተገለፀ ሲሆን ከሁሉም የፕሪምየር ሊግ እና ከ4 ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ምርጫው ተከናውኗል።

ጥሪ የተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ሰኔ 04 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ሲቀርብላቸው በቀጣይ ለሦስት ጊዜያት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚኖር ፌዴሬሽኑ አስታውቋል ።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብጠባቂዎች

ፋሲል ገ/ሚካኤል (ሰበታ ከተማ)፣ ፍቅሩ ወዴሳ (ሲዳማ ቡና)፣ አቡበከር ኑሪ (ጅማ አባጅፋር)፣ ታምራት ዳኜ (ኢትዮጵያ መድን)

ተከላካዮች

ኃይለሚካኤል አደፍረስ (ሰበታ ከተማ)፣ አማኑኤል እንዳለ (ሲዳማ ቡና)፣ ኃይሌ ገ/ትንሳይ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ መናፍ ዐወል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሰለሞን ወዴሳ (ባህር ዳር ከተማ)፣ አማኑኤል ተርፉ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፀጋሰው ድማሙ (ሀድያ ሆሳዕና)፣ ወልደአማኑኤል ጌቱ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ኢያሱ ለገሰ (አዲስ አበባ ከተማ)

አማካዮች

አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ (ሰበታ ከተማ)፣ በረከት ወልዴ (ወላይታ ድቻ)፣ አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ወንድማገኝ ኃይሉ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ያሬድ ታደሰ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ብርሀኑ አሻሞ(ሲዳማ ቡና)፣ ኪሩቤል ኃይሉ (ፋሲል ከነማ)፣ ሬድዋን ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ዊልያም ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ኤርሚያስ በላይ ( አርባምንጭ ከተማ)

አጥቂ

ዱሬሳ ሹቢሳ (ሰበታ ከተማ)፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)፣ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ (ፋሲል ከነማ)፣ ዓለምብርሀን ይግዛው (ፋሲል ከነማ)፣ ብሩክ በየነ (ሀዋሳ ከነማ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከነማ)፣ ቸርነት ጉግሳ (ወላይታ ድቻ)፣ ስንታየሁ መንግሥቱ (ወላይታ ድቻ)፣ ቤካም አብደላ (ጅማ አባ ጅፋር)፣ አብዲሳ ጀማል (አዳማ ከተማ)፣ ሙኽዲን ሙሳ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ደስታ ዋሚሾ (ሀዲያ ሆሳዕና)