“እዚህ ቦታ እንድቆም ላደረጉልኝ ውድ ተጫዋቾቼ ምስጋና ይድረስ” – ሥዩም ከበደ

የዘንድሮ የውድድር ዘመን ኮከብ አሠልጣኝ ተብለው የተመረጡት አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ የተሰማቸውን ስሜት አጋርተዋል።
የፋሲል ከነማው ዋና አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ቡድናቸውን ሻምፒዮን በማድረጋቸውም ከአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የዋንጫ እና 2 መቶ ሺ ብር ሽልማት ተቀብለዋል። አሠልጣኙም ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ተከታዩን አጭር ሀሳብ ሲናገሩ ተደምጧል።

” በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሠግናለሁ። ይሄንንም ከፍተኛ ክብር በቅርቡ ላረፈችው ወላጅ እናቴ ይሁንልኝ። ዛሬ እዚህ ቦታ እንድቆም ላደረጉልኝ ውድ ተጫዋቾቼም ምስጋና ይድረስ። ከዚህ በተጨማሪም በውጣ ውረዶች ውስጥ የነበሩትን የአሠልጣኝ ቡድን አበላት አመሰግናለሁ። ከዚህ ውጪ የክለቡን የቦርድ አባላት እና ታናሽ ወንድሜ መላኩ ከበደን አመሠግናለሁ።” ብሏል።


ያጋሩ