በጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ ሲመራ የነበረው ወላይታ ድቻ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ቀጥሯል፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን 33 ነጥቦችን በመያዝ በስምንተኝነት ያጠናቀቀው ወላይታ ድቻን በጊዜያዊነት አቶ ምትኩ ኃይሌ ቦታውን ሸፍነው ለጥቂት ወራት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን አሁን ደግሞ አቶ ወንድሙ ሳሙኤልን በቋሚነት ቀጥሯል፡፡ የስፖርት ሳይንስ የማስተርስ ምሩቅ የሆኑት አቶ ወንድሙ ከመምህርነት ባለፈ በደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ሲሰሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
አቶ ወንድሙ ሳሙኤል የጦና ንቦቹ ሥራ አስኪያጅነት መንበር ላይ በመሰየም ከአሰፋ ሆሲሶ፣ ኢያሱ ነጋ እና ምትኩ ኃይሌ በመቀጠል አራተኛው ግለሰብ ሆነዋል።