አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዲያ ሆሳዕና

የ24ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን የረፋድ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ አሰናድነተናል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ይዞት ከየገባው አሰላለፍ በከነዓን ማርክነህ ምትክ አቤል እንዳለ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን አሰልጣኝ ፍራንክ ናታልም ለኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ጨዋታ ቢሆንም ከየጨዋታው ነጥብ ማሳካት ዋና ትኩረታቸው እንደሆነ ጠቁመው ካለፉት ጨዋታዎች የተለየ አቀራረብ ይዘው እንደማይቀርቡ ገልፀዋል።

ሀዲያ ሆሳዕና ከሰበታው ጨዋታ በሁለት ተጫዋቾች ላይ ለውጥ አድርጎ የሚቀርብ ሲሆን ድንቅነህ ከበደ እና ግብ ጠባቂው ስንታየሁ ታምራት ለመጀመርያ ጊዜ ጨዋታ በሚጀምሩት ካሌብ በየነ እና ግብ ጠባቂው ያሬድ በቀለ የሚተኩ ይሆናል። አሰልጣኝ ኢያሱ መርሐፅድቅ ካለፉት ጨዋታዎች የተሻለ አቀራረብ እንደሚኖራቸውም ጠቁመዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሤ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
14 ሄኖክ አዱኛ
6 ደስታ ደሙ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
2 አብዱልከሪም መሀመድ
5 ሐይደር ሸረፋ
26 ናትናኤል ዘለቀ
18 አቤል እንዳለ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
7 ሳላዲን ሰዒድ

ሀዲያ ሆሳዕና

1 ያሬድ በቀለ
39 ካሌብ በየነ
15 ፀጋሰው ድማሙ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
17 ሄኖክ አርፌጮ
48 ክብረዓብ ያሬድ
11 ሚካኤል ጆርጅ
29 እንዳለ ዓባይነህ
7 ዱላ ሙላቱ
12 ዳዋ ሆቴሳ
26 ደስታ ዋሚሾ