ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱ ኮከቦቹን ሊሸልም ነው

ኢትዮጵያ ቡና እግርኳስ ክለብ በስሩ የሚገኙ ቡድኖች ውስጥ ላሉ እና ለቡድኖቹ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅና ለመስጠት ዝግጅት ማሰናዳቱ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ከሚሳተፈው ዋናው የእግርኳስ ቡድን በተጨማሪ ሦስት ቡድኖችን (የሴቶች፣ ከ20 ዓመት በታች እና ከ17 ዓመት በታች) የሚያስተዳድረው ክለቡ በ2013 የውድድር ዓመት ቡድኖቹ ያሳለፉትን ጊዜ በተመለከተ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 5 በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጤዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ለብዙሃን መገናኛዎች ከ7 ሰዓት ጀምሮ ከሚሰጠው መግለጫ መጠናቀቅ በኋላም ክለቡ በውድድር ዓመቱ ለታዩ ኮከቦች የሽልማት አሠጣት መርሐ-ግብር ከ10 ሰዓት ጀምሮ በዛው ቦታ (ስካይ ላይት ሆቴል) እንደሚያከናውን ተገልጿል።

በሽልማት መርሐ-ግብሩም በሁለቱም ፆታዎች እና በሁሉም እርከን የሚጫወቱ ኮከብ ተብለው የሚመረጡ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና ለቡድኖቹ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋዕኦ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና እንደሚሰጥ ሰምተናል።