ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

አሰልጣኝ መሠረት ማኒ ለተጨማሪ ዓመታት በክለቡ ለመቆየት በዛሬው ዕለት ፊርማዋን አኑራለች፡፡

ዘንድሮ በአንደኛ ዲቪዚዮን ብርቱ ተፎካካሪ በመሆን አራተኛ ሆኖ አመቱን ያገባደደው ክለቡ ሰኔ 30 ውሏ የሚጠናቀቀውን አሰልጣኝ መሠረት ማኒን ኮንትራት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት አራዝሟል፡፡ ከ2011 አጋማሽ ጀምሮ ክለቡን በማሰልጠን ላይ የምትገኘው አሰልጣኟ በተሻለ ጥቅማጥቅም እና የደመወዝ ማሻሻያ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ክለቡን ዳግም እንድትመራ በዛሬው ዕለት መፈራረሟን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

አሰልጣኝ መሠረት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በፊት ድሬዳዋ ከተማን በወንዶች እና በሴቶች፣ አዲስ አበባ ከተማን እና የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠኗ ይታወቃል፡፡