ወላይታ ድቻ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

የጦና ንቦቹ ያልተጠበቀ የአዲስ አሰልጣኝ ሹመትን ፈፅመዋል፡፡

የ2013 የውድድር ዘመንን በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ መሪነት ዓመቱን የጀመሩት ወላይታ ድቻዎች ከነበረባቸው ደካማ ውጤት መነሻነት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን በመቅጠር እጅግ ተሻሽለው ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ አሰልጣኝ ዘላለም ሺፈራው ከቡድኑ ጋር ይቀጥላሉ ተብሎ ቢጠበቅም መስማማት ባለመቻላቸው ከውድድር ዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ በጅማ አባ ጅፋር የቆዩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በቦታው ተክተዋል፡፡

የቀድሞው የትራንስ ኢትዮጵያ፣ ሐረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ወልዋሎ እና ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ለአንድ ዓመት በክለቡ እንደሚቆዩ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡