ሴካፋ 2021| የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቧል

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የሴካፋ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆነው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ ማቅረቡ ተገልጿል።

ከሰኔ 28 – ሐምሌ 12 ድረስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር በ12 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል እንደሚደረግ ይታወቃል (አዲስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ)። በውድድሩ የሚሳተፉት ብሔራዊ ቡድኖችም የቀጠናው ፍልሚያ ከመጀመሩ ከሦስት ሳምንታት በፊት ጀምሮ የተጫዋቾቻቸውን ስብስብ እያሳወቁ ይገኛሉ። አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅት መጀመሯ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለ40 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉ ተገልጿል።

በሞርሊ ባይኩዋሶ ዋና አሠልጣኝነት የሚመራው ቡድኑም ከመረጣቸው 40 ተጫዋቾች 37ቱ ከ23 ዓመት በታች እንደሆኑ ታውቋል። ህጉ በሚፈቅደው መሠረትም ሦስት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ተካተዋል። አጠቃላይ ቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ደግሞ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ዋቴንጋ ኢስማኤል (ከቺፓ ዩናይትድ) እና ሌላው ግብ ጠባቂ ቻርለስ ሉክዋንጎ (ከኬሲሲኤ)፣ አጥቂው ዩኑስ ሴንታሙ (ከቫይፐርስ)፣ ተከላካዩ ሙሩሺድ ጁኮ (ከኤክስፕረስ) እንዲሁም አማካዩ ሰዒዲ ኬይዩን (አልተገለፀም) ናቸው። ከእነዚህ አምስት ተጫዋቾች ውስጥም ሦስቱ በመጨረሻዎቹ የ23 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ እንደሚካተት በመረጃው ተመላክቷል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ከነገ በስትያ ሜንጎ የሚገኘው የዩጋንዳ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ቢሮ ተገናኝተው ውድድሩ እስኪጀምር መቀመጫቸውን አድርገው በሚዘጋጁበት እና ኪሳሲ ወደሚገኘው ክሬንስ ፓራዳይዝ ሆቴል እንደሚያቀኑ ተገልጿል። በስብስቡም ስድስት ግብ ጠባቂዎች፣ አስራ አንድ ተከላካዮች፣ አስር አማካዮች እና አስራ ሦስት አጥቂዎች

የተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ዋቴንጋ ኢስማኤል (ከቺፓ ዩናይትድ)፣ ቻርለስ ሉክዋንጎ እና ሀሰን ሙዮምባ (ከኬሲሲኤ)፣ ኦቲም ዴኒስ (ከኤክስፕረስ)፣ ኬኒ ሰዒዲ (ከቪላ)፣ ኪቦዋ ኤሪክ (ከዩፒዲኤፍ)

ተከላካዮች

ኪዚቶ ሙግወሪ ጋቪን (ከቪላ)፣ ቤጊሳ ጀምስ ፔንዝ (ከዩፒዲኤፍ)፣ ዋሉሲምቢ ኢኖክ (ከኤክስፕረስ)፣ ካዮንዶ አብዱ አዚዚ (ከቫይፐርስ)፣ ንዳሂሮ ዴሪክ (ከቪላ)፣ ካዱ ጆርጅ (ከዋኪሶ ጌንትስ)፣ ጁኮ ሙሩሺደረ (ከኤክስፕረስ)፣ ሙሳ ራመታን (ከኬሲሲኤ)፣ ሲማኩላ ኬኔዝ (ከቡል)፣ ማጋምቦ ፒተር (ከኬሲሲኤ) እና ሙኩንዳኔ ሂላሪ (ከምባራራ ሲቲ)

አማካዮች

ባያሩሀንጋ ቦቦሲ (ከቫይፐርስ)፣ ኪጉንዱ ዴሪክ (ከሶልቲሎ ብራይት ስታርስ)፣ ዋታምባላ አብዱል ካሪም (ከቫይፐርስ)፣ ኬይዩን ሰዒዲ (አልተገለፀም)፣ ሴርዋዳ ስቴቨን (ከኬሲሲኤ)፣ ሴንዮኖ ሀሰን (ከዋኪሶ ዩናይትድ)፣ አኑካኒ ብራይት (ከኬሲሲኤ)፣ ሙጉሉሲ አይሳም (ከቡሶጋ ዩናይትድ)፣ ካቦንጌ ኒኮላስ (ከቪላ) እና ሳሊም አብደላህ (ቪላ)

አጥቂዎች

ቦገሪ ኢቫም (ከዋኪሶ ጌንትስ)፣ ማሴርካ ሳዳም (ከቪላ)፣ ፖሎቶ ጁሊየስ (ከኬሲሲኤ)፣ ባሳንግዋ ሪቻርድስ (ከቫይፐርስ)፣ ይጋ ናጊብ (ከቫይፐርስ)፣ ኪዋኑካ ሀኪም (ከፕሮሊን)፣ ሴንታሙ ዩኑስ (ከቫይፐርስ)፣ ካኮዛ ዴሪክ (ከፖሊስ)፣ ሴንዮኖ ሳሙኤል (ከኬሲሲኤ)፣ አናኩ ሳዳት (ከኬሲሲኤ)፣ ሴቡፉ ፍራንክ (ከዋኪንሶ ጌንትስ)፣ ካምባሌ ኤሪክ ኬንዞ (ከኤክስፕረስ) እና ሉዋንጋ ቻርልስ (ከኬሲሲኤ)