ከአስራ ስድስት ቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የምትሳተፈው ብሩንዲ ለተጫዋቾቿ ጥሪ ማቅረቧ ተገልጿል።
በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለሁለት ሳምንታት የሚካሄደው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ ጀምረዋል። ከሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች ቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቦ ዝግጅቱን መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን የውድድሩ የ15 ጊዜ አሸናፊ ዩጋንዳም ለ40 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርባ በነገው ዕለት ዝግጅቷን እንደሚጀምር በትላንትናው ዕለት ዘግበናል። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ የቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል።
የብሩንዲ ከ23 ዓመት በታች ስብስቡ በዋናው የብሔራዊ ብድን አሠልጣኝ ጂሚ ንዳይዜዬ እየተመራ ለ29 የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል። አሠልጣኙም ከ29ኙ የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች በተጨማሪ 22 በውጪ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ጠርተዋል። በሀገር ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው :-
ዋንሲሚ ሩኩንዶ (ከሚሴጀር ንጎዚ)፣ ፓቴንት ንዲኩሪዮ (ከካያንዛ ዩናይትድ)፣ ኢስማኤል ዊሎና (ከሙሶንጋቲ)፣ ብላንቻርድ ንጋቦንዚዛ (ከአይግል ኖር)፣ ሄነሪ ሙሳጋ (ከአይግል ኖር)፣ ናርሲሴ ማሱዲ (ከአይግል ኖር)፣ አስማን ንዲኩማና (ከአይግል ኖር)፣ ካሪም አብዶል ባራንዶንዴራ (ከፍላምቡ ዱ ሴንተር)፣ ቤኒ አይራኮዜ (ከፍላምቡ ዱ ሴንተር)፣ መሐመድ ጁማ (ከፍላምቡ ዱ ሴንተር)፣ ፓፕሌ ራህማ ሩኩንዶ (ከፍላምቡ ዱ ሴንተር)፣ ሄርቭ መሐመድ (ከካያንዛ ዩናይትድ)፣ ክሪስቲያን አይሚ ካንያሙንዛ (ከካያንዛ ዩናይትድ)፣ ቻርለስ ቡምዌ (ከካያንዛ ዩናይትድ)፣ ፍሌቨር ኢንጋቢሬ (ከካያንዛ ዩናይትድ)፣ አብዲ ንዳይኬዛ (ከሙሶንጋቲ)፣ ፍራንክ ንዱዊማና (ከሙሶንጋቲ)፣ ሙሳ ሙርያንጎ (ከሙሶንጋቲ)፣ አርቶር ኒቢኮራ (ከሚሴጀር ንጎሲ)፣ አርመል ኢዛ (ከሚሴጀር ንጎሲ)፣ ጆሴፍ ካሺንዲ (ከሚሴንጀር ንጎዚ)፣ አዶልፍ ሀኪዚማና (ከሚሴንጀር ንጎዚ)፣ ኤሪክ ምቢሪዚ (ከኢንተር ስታርስ)፣ አዶልፍ ንጋቢራኖ (ለአትሌቲኮ አካዳሚ)፣ ዳኒ ንዲኩማና (ከአትሌቲኮ አካዳሚ)፣ ሁበርት አይሳ ንሳቢማና (ከሙሶንጋቲ)፣ ኢስማኤል ንሺሚሪማና (ከሩኪንዞ)፣ ቴረንስ ሩኩንዶ እና ዳርሲ ንሺሚሪማና (ከሮያል)
ከላይ ከተጠቀሱት የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች በተጨማሪ አሠልጣኝ ጂሚ ንዳይዜዬ 22 የብሩንዲ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን የጠሩ ሲሆን ከቤልጂየም፣ ኔዘርላንድ፣ እንግሊዝ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከፈረንሳይ፣ ሲውድን እና ጀርመን ሊጎች የተገኙ መሆናቸው ታውቋል። እነርሱም :-
አላዲን ቢዚማና (ከዋርናንት , ቤልጂየም)፣ አንዋር ትሪሶር (ከፔሊካን, ኔዘርላንድስ)፣ ጆርዲስ ንታማጊሮ (አልተገለፀም)፣ አሞሮስ ንሺሪማና (ከዊሌም 2 , ኔዘርላንድ)፣ ጃሚር ናውትስ (ከስፓርታን 20, ኔዘርላንድስ)፣ ጁድጊንግ ጁዴ (ከቪርቱስ , ኔዘርላንድስ)፣ ሁሴን ዩዊማና (ከካርሊስል ዩናይትድ , ኢንግላንድ)፣ ኒህ ኒዮንግሬ (ከኤክረን , ቤልጂየም)፣ ፕሪንስ ኒዮንገሬ (ግሮኔንሆክ ,ቤልጅየም)፣ ሄንድሪክስ ንዲኩማና (ሎቬሬ ሴንተር ,ቤልጅየም)፣ ኦሊቨር ኒጋባ (ሬድ ሪቨር ,አሜሪካ)፣ ክሪስ ኢንጋንጂ (ኒውዮርክ, አሜሪካ)፣ አይሜ ባንዳ (ሳንስ ,ፈረንሳይ)፣ ኒኮላስ ካሲራሀምዌ (ሞይራንስ ,ፈረንሳይ)፣ ኪን ቦዮዮ ( ሞይራንስ ,ፈረንሳይ)፣ ሂላይሬ ኦባሜ (ስታደልሆፈን ,ጀርመን)፣ ዩሱፍ ሀሰን (ኒውዮርክ ,አሜሪካ)፣ ጀስቲን ማሱዲ (ዳኮታ ፊውዥን ,አሜሪካ)፣ ሸሪፍ ኢኔዛ (ኒኮፒንግ ,ስዊድን)፣ ጀስቲን ሩሂምባዛ (ሎንስታር ,አሜሪካ)፣ አንዲ ዳዌ (ቶንገረን ,ቤልጅየም) እና ክሪስፓልዲንሆ ቹባካ (ቫርሌይን ,ቤልጅየም)
ትናንት ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾችም ከዛሬ ጀምሮ በዩሩኩንዶ ስታዲየም ልምምድ እንደሚጀምሩ ተመላክቷል።