ሴካፋ 2021 | ተጋባዧ ሀገር ለተጫዋቾቿ ጥሪ አቅርባለች

አስራ ሁለት ሀገራት በሚወዳደሩበት የሴካፋ ውድድር ላይ በተጋባዥነት የምትሳተፈው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለተጫዋቾቿ ጥሪ ማድረጓ ተገልጿል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሰኔ 26 – ሐምሌ 12 ድረስ በሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር ላይ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች ስብስባቸውን እያሳወቁ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ እና ቡሩንዲ ስብስባቸውን ማሳወቃቸውን የገለፅን መሆኑ ሲታወስ አሁን ደግሞ በተጋባዥነት በውድድሩ የምትሳተፈው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጓ ታውቋል።

በአዲሱ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ዧን-ክሎድ ሎቦኮ የሚመራው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ስብስብ በሀገር ውስጥ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከቻይና፣ ቤልጂየም፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ሞሮኮ ሊጎች የተመረጡ ተጫዋቾችም አካቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ የቀረበላቸው ጀርሚ ንጋኪያ፣ ሁበርት ምቡይ እና ኦስካር ማሪቱ የቡድኑን የፊት መስመር በጥሩ ሁኔታ እንደሚመሩ እምነት ተጥሎባቸው ስብስቡ ውስጥ መኖራቸውም ተመላክቷል። በተጨማሪም በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በነበረው የማጣሪያ ጨዋታ ከዋናው ቡድን ጋር የተሳተፉት ናታን ኢዱምባ፣ ሲል ኢቤንጎ እና ካሪም ኪምቪዊዲ በአሠልጣኝ ዧን-ክሎድ ሎቦኮ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

በቅርቡ ዝግጅት እንደሚጀምሩ የተገለፀላቸው 30 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው :-

ግብ ጠባቂዎች (3)

ሚኬል ሉያምቡላ (ከሉቤክ , ጀርመን)፣ ብሩዴል ኢፎንጌ (ከጄ ኤስ ኬ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ሄኖክ ካማላንድዋኮ (ከዲ ሲ ኤም ፒ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)

ተከላካዮች (10)

ጀረሚ ንጋኪያ (ከዋትፎርድ , እንግሊዝ)፣ ስቴቨን ኤቡዌላ (ከማኒማ ዩኒየን , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ሄኖን ማንጊንዱላ (ከዲ ሲ ኤም ፒ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ቤኒ ዋሀላ (ከኤ ኤስ ቪ. ክለብ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ጋል ካኩጂ (ከሴራይንግ , ቤልጂየም)፣ ሁበርት ምቡይ (ከሆፈንየም , ጀርመን)፣ ኦርቲኔል ማዋዉ (ከዲን ቦስኮ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ናታን ኢዱምባ ፋሲካ (ከሴንት-ኢሎይ ሉፖፖ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ጆን ንካዲዮ (ከስታንዳርድ ሌዥ , ቤልጂየም) እና ንታምብዌ ካሎኒ (ከቲፒ ማዜምቤ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣

አማካዮች (8)

ቤቭርሊ ማካንጊላ (ከኮሎራዶ , አሜሪካ)፣ ሮሊ ባሉምቢ (ከኤ ኤስ ቪ. ክለብ, ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ክርስቲያን ንሱንዲ (ከዲ ሲ ኤም ፒ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ካሪም ኪምቪዊዲ (ከዲ ሲ ኤም ፒ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ምፒያ ንዜንጊሌ (ከማኒማ ዩኒየን , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ኢፋሶ ኢፉንጋ (ከዲፋ ኤል ጃዲዳ , ሞሮኮ)፣ ዊሊያም ባሊክዊሻ (ከስታንዳርድ ሌዥ , ቤልጂየም)፣ ሲል ኢቤንጎ (ከሉፖፖ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)

አጥቂዎች (9)

ኔልሰን ባሎንጎ (ከሴንት ትሮንድ , ቤልጂየም)፣ ጆይል ቤያ (ከቲፒ ማዜምቤ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ኦቶስ ቤሌኬ (ከቲፒ ማዜምቤ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ አይሳክ ሺባንጉ (ከቲፒ ማዜምቤ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ኤሪክ ካብዌ (ከኤ ኤስ ቪ. ክለብ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ማይካ ንጋሊና (ከኮሎራዶ , አሜሪካ)፣ ላውረንት ንታምብዌ (ከብለሲንግ , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)፣ ኦስካር ማሪቱ (ከቻንግዙ ማይቲ ላዮን , ቻይና) እና ምቢዲ ምባላ (ከሉቡምባሺ ስፖርት , ዲሞክራቲክ ኮንጎ)