የስድስት ክለቦች ውድድር የሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው ተዘጋጅተዋል።
በመጀመሪያው የውድድሩ ጨዋታ ድል የቀናቸው አዳማ ከተማ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ከደቂቃዎች በኋላ የሚያደርጉት የእርስ በእርስ ጨዋታ እጅግ ትልቅ ግምት አግኝቷል። የአዳማ ከተማው አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ካሸነፉበት ቋሚ ስብስብም አንድ ተጫዋች ብቻ ቀይረዋል። በዚህም ታፈሰ ሰርካ ወጥቶ ሠይፈ ዛኪር ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል።
በተመሳሳይ በመጀመሪያው ጨዋታ ሀምበሪቾን አንድ ለምንም ረቶ ለዛሬው ጨዋታ የቀረበው የአሠልጣኝ መሐመድኑር ኮልፌ እንደ ተጋጣሚው አዳማ አንድ ተጫዋች ብቻ በመቀየር ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ዳዊት ቹቹን ተክቶ ተመስገን ዘውዱ ተሰልፏል።
በዚህ ጨዋታ ወንድማማቾቹ አሚን ነስሩ እና ፉአድ ነስሩ በተቃራኒ ይፋለማሉ።
ፌዴራል ዋና ዳኛ ሄኖክ አክሊሉ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ይመሩታል። የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ የሚከተለው ነው።
አዳማ ከተማ
1 ሴኩባ ካማራ
20 ደስታ ጊቻሞ
80 ሚሊዮን ሰለሞን
28 አሚን ነስሩ
27 ሠይፈ ዛኪር
5 ጀሚል ያቆብ
88 አሊሴ ጆናታን
8 በቃሉ ገነነ
26 ኤልያስ አህመድ
9 በላይ ዓባይነህ
31 ማማዱ ኩሊባሊ
ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ
1 አዲስኪዳን ኪዳነማርያም
5 ፈቱ አብደላ
3 አቡበከር ከሚል
13 ፉአድ ነስሩ
21ተመስገን ዘውዱ
11 ኪሩቤል ወንድሙ
2 አቡበከር ሸሚል
8 ደሳለኝ ወርቁ
7 አንዋር ዱላ
9 ሀቢብ ከማል
10 ብሩክ ሙሉጌታ