ሐምሌ 10 በባህር ዳር ስታዲየም የሚጀምረው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈለው የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቧል።
ነገ እንደሚጀምር ቀድሞ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት በሌላ ውድድር ላይ እየተሳተፉ መሆኑን እና የዝግጅት ጊዜ ማጠሩን ተከትሎ የመጀመሪያው ጊዜ ለሁለት ሳምንት ተራዝሟል። እንደተጠቀሰው በሌላ ውድድር ላይ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ደቡብ ሱዳን በኳታር የአረብ ሊግ ውድድሯን አጠናቃ ትናንት አመሻሽ ጁባ ገብታለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ከትናንት በስትያ በ2020 ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑን በሴካፋ ውድድር ላይ ወስዶ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ያደረገው አሠልጣኝ ሲሞን ጀምስ ዮር በኢትዮጵያ በሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈለውን የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን እንዲያሰለጥን ተሹሟል።
ከአንድ ቀን በፊት መንበሩን ያገኙት አሠልጣኝ ሲሞን ጀምስ ዮር ትናንት ደግሞ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅታቸውን ለመጀመር ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል። በአሠልጣኙ ጥሪ ሦስት ግብ ጠባቂዎች፣ አስር ተከላካዮች፣ አስር አማካዮች እንዲሁም ስምንት አጥቂዎች ተካተዋል። በስብስቡ ውስጥ ከተካተቱ የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች በተጨማሪም አምስት በዩጋንዳ፣ ሁለት በኬንያ እና ሁለት በሱዳን ሊጎች ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾች መኖራቸው ታውቋል።
አሠልጣኝ ሲሞን ጀምስ ዮር ለሴካፋ ውድድር የጠሯቸው 31 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው:-
ግብ ጠባቂዎች
ረመዳን ጆን ማይክ (ከማላኪያ ,ጁባ)፣ ኢማኑኤል ቶቢ (ከማላኪያ ,ጁባ) እና ኔልሰን ቶምቢ (ከማላኪያ ,ጁባ)
ተከላካዮች
ዶሚኒክ ጀምስ (ከካቶር , ጁባ)፣ ዳሃታ ጆሴፍ ስቴፈን (ከቫይፐርስ ስፖርት ,ዩጋንዳ)፣ ቤንጃሚን ላኩ (ከጀሙስ ,ጁባ)፣ ሳዳም አደም (ከጉዴሌ ,ጁባ)፣ ሳሙኤል አይሳክ (ከጉዴሌ ,ጁባ)፣ ዴቦ ጁሉሱሶስ ሞሮ (ከማላኪያ ,ጁባ)፣ ሬሃን አንገር ማሎንግ (ከሙኑኪ ,ጁባ)፣ ኦማን ሞቢል አጎግ (ከማላኪያ ,ጁባ)፣ ሳሙኤል ታባን ማሊስ (ከካቶር ,ጁባ) እና ኦሞት ሴቢት (ከአማል አትላባር ,ሱዳን)
አማካዮች
ስቴፈን ፓዋር (ከሙኑኪ ,ጁባ)፣ ዊሊያም ጋማ ኢማኑኤል (ከማላኪያ ,ጁባ)፣ ኦማር ላውቴ ሚካኤል (ከአማራት ዩናይትድ ,ጁባ)፣ ጆሴፍ ማሊሽ (ከካቶር ,ጁባ)፣ ሞትዋኪል አብዱላካሪም (ከአትላባራ ,ጁባ)፣ ዳንኤል ሳሙኤል (ከአል ማሪክ ,ጁባ)፣ ማንዴላ ማሊሽ (ከአትላባር ,ጁባ)፣ ዶሚኒክ አንጄሎ (ከሙኑኪ ,ጁባ)፣ አሳድ ሙሳ አብደላ (ከሊዮፓርድስ ,ኬንያ) እና ጆን ጁሉክ ማንያንግ (ከሆሊ ፋሚሊ ,ሩምቤክ)
አጥቂዎች
ቢዳ ኢዝራ ኢሊ (ከኬይቱሜ ,ዩጋንዳ)፣ ሎኪ ኢማኑዌል ፒተር (ከሶልቲሎ ብራይት ስታር ,ዩጋንዳ)፣ ጆዋንግ ኢማኑዌል ካካ (ከማላኪያ ,ጁባ)፣ ጆርጅ ኦገስቲኖ ላዱ (ከሙኑኪ ,ጁባ)፣ ዳኒ ሉዋል ጉማኖክ (ከማታር ,ኬንያ)፣ አሉክ አኬክ ማቢዮር (ከአማል አቲያባራ ,ሱዳን)፣ ሙኬይት ውል አኬን (ከምባራራ , ዩጋንዳ) እና ዋኒ ኢቫንስ (ከቡሶጋ ዩናይትድ , ዩጋንዳ)