አብዱልከሪም መሐመድ የመጀመሪያው የዐፄዎቹ ፈራሚ ሆኗል

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነው ፋሲል ከነማ የመስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሐመድን አስፈርሟል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ አራት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሐመድ በደቡብ ፖሊስ የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኃላ ለሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ቡና ከተጫወተ በኋላ በ2010 ነበር ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው። በዛው ዓመት የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው አብዱልከሪም ለሁለት ዓመት ለዐፄዎቹ መፈረሙን ተጫዋቹ እና የተጫወቹ ወኪህ አዛርያ ተስፋፅዮን እንዲሁም ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡