አንደኛውን የማሟያ ውድድር አላፊ ክለብ የሚለየውን ጨዋታ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች እንዲህ አጠናክረናል።
በአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሚመራው ጅማ አባጅፋር ጥሩ ሆኖ ካየበት እና ሦስት ነጥብ ካገኘበት የኮልፌ ጨዋታ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም ዋውንጎ ፕሪንስ ወጥቶ ሱራፌል ዐወል ወደ ሜዳ ገብቷል።
በተቃራኒው በአራተኛ ዙር ጨዋታ የማሟያ ውድድሩ ቀዳሚ አላፊ ቡድን መሆኑን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ በበኩሉ ሦስት ለውጦችን አድርጓል። በዚህም አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ሠይፈ ዛኪር፣ አሚኑ ነስሩ እና ሚሊዮን ሠለሞንን አሳርፈው ላሚን ኩማሬ፣ እዮብ ማቲዮስ እና ታፈሰ ሠርካን በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል።
ፌዴራል ዋና ዳኛ ዳንኤል ግርማይ በሚመሩት ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ የሚጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።
ጅማ አባ ጅፋር
91 አቡበከር ኑሪ
28 ስዩም ተስፋዬ
16 መላኩ ወልዴ
3 አሌክስ አሙዙ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረስላሴ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
13 ዋለልኝ ገብሬ
8 ሱራፌል ዐወል
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ
አዳማ ከተማ
1 ሴኩምባ ካማራ
5 ጀሚል ያቆብ
20 ደስታ ጊቻሞ
34 ላሚን ኩማሬ
13 ታፈሰ ሠርካ
6 እዮብ ማቲዮስ
88 አሊሴ ጆናታን
8 በቃሉ ገነነ
25 ኤልያስ ማሞ
26 ኤሊያስ አህመድ
10 አብዲሳ ጀማል