ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች የተጀመረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 9ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ 7 ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡ መሪዎቹም መሪነታቸውን እንዳስጠበቁ ወደ 10ኛው ሳምንት ተሻግረዋል፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ ተቀራራቢ ደረጃ ላይ የሚገኙት ጅማ አባ ቡና እና ናሽናል ሴሚንትን ያገናኘው ጨዋታ በአባ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ናሽናል ሴሜንት በአብነት መንግስቱ ግብ ባለሜዳውን 1-0 ሲመራ ቢቆይም ተመስገን ደረሰ እና ዳዊት ተፈራ ለአባ ቡና አስቆጥረው ጅማ በምድቡ መሪነት እንዲቆይ አድርገውታል፡፡
ወደ አርሲ ነገሌ የተጓዘው አአ ከተማ 1-0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን የድል ግብ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ ዮናታን ብርሃኔ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሀላባ ከተማ ባቱ ከተማን 2-0 በማሸነፍ ወደ ደረጃ ሰንጠረዡ አናት ተጠግቷል፡፡ የሀላባን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት ዮሴፍ ዮሃንስ እና አዩ በቀታ ናቸው፡፡
ወደ አበበ ቢቂላ ስታድየም የመጡት ነቀምት ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማ ባለሜዳዎችን ድል አድርገዋል፡፡ በ7፡00 ከፌዴራል ፖሊስ የተጫወተው ሻሸመኔ ከተማ ድ ለማግኘት 90 ደቂ ተጠናቆ ጭማሪ ደቂቃ አስፈልጎታል፡፡ ለሻሸመኔ ገዛኸኝ በርገሳ ሁለት ፣ ያህያ አሎ እና ዘውዱ መና አንድ አንድ ሲያስቆጥሩ ለፌዴል ፖሊስ ሄኖክ አሰፋ በአወዛጋቢ ፍፁም ቅታት ምት እና በጨዋታ እንዲሁም ቻላቸው ቤዛ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ነቀምት አአ ዩኒቨርሲቲን 3-0 በተረታበት ጨዋታ ደግሞ አብርሃም ጫላ ፣ ማንያዘዋል ጉዲሳ እና ተስፋሁን ዳንኤል ለነቀምት አስቆጥረዋል፡፡
ነገሌ ቦረና ጅንካን 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት በድንገተኛ ሀዘን ምክያት ጨዋታ ላላደረገው ነገሌ ቦረና ልማደኛው ዳግም በቀለ ብቸኛዋን የማሸነፍ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ወራቤ ከተማ በአሸናፊነት ቀጥሎ ደቡብ ፖሊስን 2-1 አሸንፏል፡፡ በጨዋታው መሃል በተፈጠረ ውዝግብ ለተወሰኑ ደቂዎች ተቋርጦ በነበረው ጨዋታ ካሳ ከተማ እና ፈድሉ ሃምዛ ለወራቤ ከተማ የድል ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ለደቡብ ፖሊስ ሐብታሙ ገዛኸኝ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡
ትላንት በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ድሬዳዋ ፖሊስ ጅማ ከተማን 3-1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡
የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል፡-
ፎቶ – ሻሸመኔ ከተማ