ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከሰሞኑ የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል አስቀድሞ ማደስ የቻለው ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ጋዲሳ መብራቴ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በደደቢት የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኃላ ለኒያላ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ያለፉትን አራት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው አማካዩ ወደ ምስራቁ ክለብ አምርቷል፡፡

ሌላኛው ፈራሚ እንየው ካሣሁን ነው፡፡ የቀድሞው የፌዴራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ወልዋሎ የመስመር ተከላካይ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ መለያ የቆየ ሲሆን ድንቅ የውድድር ዘመን ካሳለደ በኋላ የብርቱካናማዎቹ አዲስ ፈራሚ ሆኗል፡፡

ክለቡ የአዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን ዛሬ እና በቀጣይ ቀናት እንደሚያስፈርም ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡