ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ በይፋ አስፈርሟል

ተክለማርያም ሻንቆን ያጣው ኢትዮጵያ ቡና በምትኩ ተጫዋች በይፋ አስፈርሟል።

ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች የግብ ዘቡ በረከት አማረ ነው። በ2012 የውድድር ዘመን ከቡናማዎቹ ጋር ቆይቶ የነበረው በረከት ዓምና ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ እንደነበር አይዘነጋም። በኮቪድ-19 ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስም በመቐለ ቆይቶ ዘንድሮ ግማሽ ዓመት ላይ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ መጨወት ቀጥሎ ነበር።

ለአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የጨዋታ መንገድ ምቹ እንደሆነ የሚገለፀው በረከት ከደቂቃዎች በፊት የሦስት ዓመት ውል ከቀድሞ ክለቡ ጋር መፈራረሙም ታውቋል። 

ያጋሩ