ሲዳማ ቡና የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

እስካሁን ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሲዳማ ቡና የሁለት ተከላካዮቹን ውል አድሷል፡፡

ጊት ጋትኮች ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ነው፡፡ አዲስ አበባ ከተማን በመልቀቅ ሲዳማ ቡናን በ2012 በመቀላቀል ሁለት የውድድር ዓመታትን ያሳለፈው ቁመተ ረጅሙ ተከላካይ አሁንም ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ መቆየቱ ተረጋግጧል፡፡
ሌላኛው ውሉን ያራዘመው የመስመር ተከላካዩ አማኑኤል እንዳለ ነው፡፡ የሲዳማ ቡና የታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው ይህ ሁለገብ ተጫዋች ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመት በዋናው ቡድን የቆየ ሲሆን ለቀጣዩ ሁለት ዓመታት ለመዝለቅ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ያጋሩ