ፋሲል ከነማ የተከላካዩን ውል አራዘመ

አዳዲስ ተጫዋቾች እያስፈረመ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የተከላካዩ ዳንኤል ዘመዴን ውል አራዝሟል፡፡

ከፋሲል ከነማ የታችኛው ቡድን የተገኘው ይህ ተከላካይ ዘንድሮ በአብዛኛው ጨዋታዎች ላይ በተጠባባቂነት ያሳለፈ ሲሆን ፋሲል ከነማ የ2013 ቻምፒዮን መሆን ከቻለ በኃላ የመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወቱ ይታወሳል፡፡

ዳንኤል በዐፄዎቹ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ነው ውሉን ያደሰው።

ያጋሩ