ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ፡ ፋሲል ከተማ እና ወልድያ ድል ሲቀናቸው አማራ ውሃ ስራ እና መድን ወደ ላይ ከፍ ማለታቸውን ቀጥለዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 9ኛ ሳምንት 7 ጨዋታዎች  ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተደርገው ፋሲል ከተማ ከመሪው ጋር ያለውን ልዩነት መልሶ ያጠበበትን ድል አስመዝግቧል፡፡ አማራ ውሃ ስራ እና መድንም በተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻላቸውን ቀጥለዋል፡፡

ወደ ሰበታ ያቀናው ፋሲል ከተማ ሰበታ ከተማን 1-0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ የፋሲልን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ይስሃቅ መኩርያ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ድሉ ፋሲልን በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ስፍራውን እንዲያስጠብቅ አድርጎታል፡፡

ወልድያ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃንን አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል፡፡ የወልድያን ብቸኛ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው የቀድው የመከላከያ አምበል ዮሃንስ ሃይሉ ነው፡፡

አማራ ውሃ ስራ ወሎ ኮምቦልቻን አስተናግዶ 2-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ የአማራ ውሃ ስራን የድል ግቦች ፍቅረሚካኤል እና መለሰ ትዕዛዙ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የሜዳው ተጋሪ እንዲሆን የተወሰነለት ሙገር ሲሚንቶን 1-0 አሸንፏል፡፡ የመድንን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ዘንድሮ ድንቅ አቋሙን እሳየ የሚገኘው ሐብታሙ ወልዴ ነው፡፡

ቡራዩ ከተማ ሱሉልታ ከተማን አስተናግዶ 1-1 አቻ ተለያይቷል፡፡ ቡራዩ ደርብ ጎል 1-0 መምራት ቢችልም እዮብ ደረጄ ሱሉልታን አቻ አድርጓል፡፡

አክሱም ላይ አክሱም ከተማ ከባህርዳር ከተማ 1-1 ተለያይተዋል፡፡ ለባህርዳር ዳንኤል ሃይሉ ከመረብ ሲያሳርፍ  ክብሮም አጽብሃ ለአክሱም ከተማ አስቆጥሯል፡፡

አዲግራት ላይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርትን አስተናግዶ 2-2 ተለያይቷል፡፡ ለወልዋሎ አዲሱ ካሳ እና ኢሳያስ ታደሰ ሲያስቆጥሩ ለውሃ ስፖርት ኤፍሬም ቶማስ እና ዮሴፍ በቀለ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

xsjfygids

 

ፎቶ – ፋሲል ከተማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *