በሴካፋ ውድድር የመክፈቻ ቀን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይጫወታሉ

በዛሬው ዕለት የምድብ ድልድሉ የወጣው የሴካፋ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች የቀን እና ሰዓት መርሐ-ግበር ታውቋል።

ዘጠኝ ሀገራትን በሦሰት ምድብ ከፋፍሎ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። የምድብ ድልድሉ እኩለ ቀን አካባቢ የወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ የምድብ ጨዋታዎች ቀን እና ሰዓት ታውቋል። በዚህም መሠረት የውድድሩ የመክፈቻ መርሐ-ግብር በምድብ ሀ በሚገኙት ዩጋንዳ እና ፊሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መካከል እንደሚሆን ተገልጿል። ይህ ጨዋታ 8 ሰዓት ከተደረገ በኋላ ደግሞ በምድብ ሁለት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በ10 ሰዓት የምትጫወት ይሆናል።

ኢትዮጵያ ቅዳሜ 10 ሰዓት ከኤርትራ ጋር ከተጫወተች በኋላ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዋን ከስድስት ቀናት በኋላ ዓርብ 10 ሰዓት ከቡሩንዲ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

በተያያዘ ሁሉም የውድድሩ ጨዋታዎች 8 እና 10 ሰዓት እንደሚከናወኑ ለማወቅ ተችሏል።

*ሁሉንም የውድድሩን ጨዋታዎች መርሐ-ግብር ነገ ጠዋት ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

ያጋሩ