ለትክክለኛ መረጃዎች እምብዛም ክፍት ያልሆነው ሴካፋ በሀገራችን የሚጀመረው ውድድር እሁድ እንደሆነ ይፋ ቢያደርግም ውድድሩ ቀድሞ በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ሰምተናል።
በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሰኔ 26 ጀምሮ እንደሚካሄድ ከወራት በፊት ቢገለፅም “አንዳንድ ተሳታፊ ሀገራት በሌላ ውድድር ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ” የመጀመሪያው ቀን ወደ ሐምሌ 10 ተቀይሯል። እስከ ትናንት ማታ ድረስ ይህ መረጃ በብዙዎች ዘንድ የነበረ ቢሆንም ሴካፋ የምድብ ድልድሉን ካወጣ በኋላ ባሰራጨው የጨዋታ ቀን እና ሰዓት መርሐ-ግብር ላይ የውድድሩ መጀመሪያ ቀን እሁድ እንደሆነ ጠቁሞ ነበር። ነገርግን ከሰዓት የሚመለከታቸው አካላት ባደረጉት ስብሰባ የውድድሩ መጀመሪያ ቀን ቀድሞ በተያዘለት ጊዜ (ሐምሌ 10) እንደሆነ ተገልጿል። ይሄንን ተከትሎ የመክፈቻ ጨዋታዎቹ ቅዳሜ 8 እና 10 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል።
*ሴካፋ መጀመሪያ ያወጣው መርሐ-ግብር (ውድድሩ እሁድ እንደሚጀመር የገለፀበት) ከስር ተያይዟል👇