አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በሲዳማ ቡና አዲስ ስምምነት ፈፅመዋል

በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ሲዳማ ቡናን ተረክበው ቡድኑን ከመውረድ መታደግ የቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በክለቡ ውላቸውን አድሰዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከተለያዩ ክለቦች ጋር የሊጉ አሸናፊ በመሆን ደማቅ ታሪክን ማፃፍ የቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በሲዳማ ቡና ያላቸውን ቆይታ አራዝመዋል። አሰልጣኙ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በቀላሉ ግብ ይቆጠርበት የነበረውን ቡድን በሒደት በማሻሻል ብሎም ወደ ማጥቃት በሚደረጉ ፈጣን ሽግግሮች ይታወቅ የነበረውን ቡድን ወደ ቀደመው ጥንካሬው እንዲመለስ በማስቻል ረገድ እጅግ አመርቂ ሥራን መሥራት ችለዋል።

በቀጣዩ የውድድር ዘመን ሲዳማ ቡና የቀደመው አስፈሪነቱን ለመመለስ እየሰሩ የሚገኙት አሰልጣኙ ከወዲህ ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛል።

ያጋሩ