የኢትዮጵያ ቡና የቀኝ ተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ኃይሌ ገብረተንሳይ በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆየውን ውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ፈፅሟል።
በፈንሳዊው አሰልጣኝ ዲዲየ ጎሜስ ከቡድኑ የ20 ዓመት በታች ስብስብ ወደ ዋናው ቡድን የማደግ የቻለው ተጫዋቹ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በኢትዮጵያ ቡና መለያ በግሉ ጥሩ የሚባልን ጊዜ ማሳለፍ ችሏል። እርጋታ እና በራስ መተማመን የተላበሰው ኃይሌ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የአንድ ዓመት ኮንትራት ቢኖረውም በዛሬው ዕለት ለተጨማሪ ሦስት ዓመት (እስከ 2017) በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆየውን ስምምነት ፈፅሟል። ለቦታው በቀጣዩ የውድድር ዘመን ክለቡን በዛሬው ዕለት ከተቀላቀለው ሥዩም ተስፋዬ ጋር ለተሰላፊነት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ከወዲሁ ይጠበቃል።
የአጭር ጊዜ የውል ስምምነት በተለመደበት የሀገራችን የክለቦች እግርኳስ ኢትዮጵያ ቡና ዐምና በሚኪያስ መኮንን እና በአቡበከር ናስርን ለረጅም አመታት የሚዘልቅ የውል ስርአት ዘንድሮም አጠንክሮ እየቀጠለ ይገኛል ይህም ለሌሎች ክለቦች ተምሳሌት የሆነ ተግባር እንደሆነ ይታመናል።