ሲዳማ ቡና ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ረፋድ ላይ ስድስተኛ ተጫዋቻቸውን ያስፈረሙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ተጨማሪ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል።

አዲሱ ፈራሚ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተለያየው የመሐል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ነው። ከዚህ ቀደም በደደቢት ፣ አዳማ ከተማ እና መከላከያ ተጫዋውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ ባሳለፍነው የክረምቱ የዝውውር መስኮት እንዲሁ በወቅቱ በገብረመድኅን ኃይሌ ይመራ ወደ ነበረው መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ቡድኑ በሊጉ መካፈል ባለመቻሉ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ሳይጠበቅ ማምራቱ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ቡና ምንም እንኳን በቋሚነት በርራታ ጨዋታ መሰለፍ ባይችልም በቋሚነት በጀመረባቸው ጨዋታዎች ግን ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴን ማድረግ የቻለው ተከላካዩ ለሲዳማ ቡና የተከላካይ መስመር ሌላ አማራጭ እንደሚፍጥር ይጠበቃል።

ያጋሩ