የዋልያዎቹ አባላት በሙዚቃ ሥራ…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የሙዚቃ ቪዲዮ ሊሰሩ እንደሆነ ይፋ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን እና በደመራ ሚዲያና ኮሚውንኬሽን ትብብር የሚዘጋጀው ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ በዋናነት በሀገራችን እየተስተዋሉ የሚገኙ ወቅታዊ ችግሮች ለመቅረፍ የእግርኳሱን በጎ ተፅዕኖ ለመጠቀም እንዲሁም በሴካፋ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ወጣት ተጫዋቾች በቀጣይ ሀገራቸውን ለአፍሪካ ዋንጫ እንዲያበቁ አደራ ለመስጠት እንደሆነ የፌደሬሽኑ መረጃ ይጠቁማል።

በቅርቡ እንደሚለቀቅ በሚጠበቀው በዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ ስራ ላይ ናሆም ታደሰ በግጥም ፣ ፍፁም አበረ በዜማ ሲሳተፉ ቪዲዮውን ዳይሬክት በማድረግ ደግሞ የኢቢሲ የስፖርት ክፍል ባልደረባ የሆነው ንዋይ ይመር እንደተሳተፈበት ተገልጿል።

ያጋሩ