የነገ የዋልያዎቹ ጨዋታ የሰዓት ለውጥ ተደርጎበታል

በነገው ዕለት የኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጎበታል።

ሐምሌ 10 የተጀመረው 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ በደማቅ ሁኔታ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተከናወነ ይገኛል። ውድድሩም ዛሬ እረፍት ላይ የሚገኝ ሲሆን በነገው ዕለት የኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች በሚያደርጉ ግጥሚያ ይቀጥል። ይህ ጨዋታ ነገ 10 ሰዓት እንደሚደረግ ቀድሞ ቢገለፅም በባህር ዳር አመሻሽ ላይ የሚጥለው ከባድ ዝናብ 10:00 የሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ እክል እየፈጠረ በመሆኑ ለውጡን ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ጨዋታው ወደ 8 ሰዓት ተለውጧል። የሌሎች ጨዋታዎች ሰዓት ደግሞ በቀጣይ ይፋ እኖደሚደረግ ሲጠበቅ ምናልባትም 5:30 እና 8:00 እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ያጋሩ